Home > Articles > ዛሬም ተጠንቀቅ አማራ

ዛሬም ተጠንቀቅ አማራ

August 5, 2012

ስማኝ ህዝቡ ስማኝ ሀገሩ!

ስማኝ ህዝቡ ስማኝ ሀገሩ!

የገጠመህ ጠላት ይሉኝታ አያቅም ። ለአረመኔ ገዢዎችህ አይዞህ ባዮቹ የታሪክ ጠላቶችህ ደሞ ስለ ሀገርህና አንድነትህ ባለፈው ታሪክህ ያደረከው ተጋድሎ በጽኑ የተረዱት ከመሆን አልፎ የውስጥ እግር እሳት ሆኖባችው የሚኖሩ ናቸው። ባሳለፍከው 21 የመከራ ዘመን ጠላቶቿ ሀገርህ ኢትዮጵያን ከዓለም ካርታ ሊያጠፍዋት የቻሉትን ሁሉ ዶልተዋል ፣ አንተ ግን በዚህ ሁሉ መከራ መሃል ኢትዮጵያ ሀገሬ አጠፋም ብለህ ማመንህ እራሱ እንቅፋት ሁኖባቸዋል። ይህንንም እንቅፋት ለማስወግድ ፈርጀ ብዙ የሆነ ስነልቦናዊና አካላዊ ጥቃቶችን እየፈጸሙብህ ሰብአዊ ፍላጎትህን ገተው ጥቅምና መብትህን ረግጠው ከመኖር ወደ አለመኖር ጠርዝ ላይ አድደርሰውሃል።

ስማኝ ህዝቡ ስማኝ ሀገሩ!

የወቅቱ የሀገርህ ሁኔታ ዛሬም ሳትዘናጋ ተጠንቅቀህ እራስህን ከጥፋት የምትከላከልብትን መላ ማበጀት ያለብህ ወሳኝ ግዜ ነው። እንደ ከአሁን ቀደሙ ሁሉ ከበስተጀርባህ የሀገርህና ያንተን የወደፊት እጣፈንታ ለመወሰን ደፋቀናው ከጀመረ ውሎ አድሯል። እንደ ሰጋር ፈረስ የሚያፈሱላቸውን ገብስ እንጂ የሚጋልቧቸው ወዴት መሆኑን የማየትና የመረዳት አቅም የሌላቸውን የአብራክህ ክፋዮች ባንተ ስም ጭነው ወደ ምኒልክ ቤተመንግስት ሊጋልቡዋቸው በዝግጅት ላይ መሆናቸው የአደባባይ ሚስጥር ከሆነ ውሉ አድሯል።

ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም ይውደቅ እንጂ የባሰ አይመጣም ፣ አዙረህ ተመልከት የሚሉህ አፍቃሪ መንግስቱ ናቸው ፣በማለት የምታፈርሰውን የግፍ አገዛዝ በምን አይነት የተሻለ ስርዓት እንደምትተካ እንዳታስብና እንዳትዘጋጅ በማዘናጋት ለንዶን ላይ ከጀርባህ በማሴር ለዛሬው የሰቆቃ ኑሮ በመዳረግ በራስህ እምነት አተህ ባርነትን አሜን ብለህ ትቀበል ዘንድ ከትግሬ ጎጠኞች ጋር በማበር ስነልቦናዊና አካላዊ ጥቃት የፈጸመብህ ኃይል ዛሬም ለሌላ ዙር ጥቃት አድብቷል። የጠገበውን ጎጠኛ በተራበ ጎጠኛ በመተካት የይስሙላ ለውጥ በማሳየት ዐማራና አማርኛን ጨርሶ ለማጥፋት ግዜ ለመግዛት ወስኗል። ትግልህ በመለስ ዜናዊ መኖር አለመኖር ዙሪያ እንዲያጠነጥን ስርነቀል ይዘት እንዳይኖረው የማደናገርያ ፖለቲካዊ ቀመሮች በአዳዲስ ተዋንያን ከተዘረጋልህ ሰንበትበት ብሏል። የግፍ አገዛዙ ቁንጮ መለስ ዜናዊ ሞቶም ይሁን ታሞ ለረጅም ጊዜ ከሕዝብ ተሰውሮ ባለበት ሁኔታ መታመሙን እንኩዋን ከአፍሪካዊ መረ ነው በምክንያት መስማት የተቻለው ።የማዕራቡ ሀገሮች ሚዲያዎችም ሆኑ የምዕራብያውያኑ መንግስታት በአደባባይ የአልሰማንም አላየንም አይነት ዝምታ ምንያህል ላንተ ካላቸው ፍራቻና ጥላቻ የተነሳ መሆኑን መገመት አያዳግትም። ምዕራባውያኑ ትግልህን ሊያጎለብት የሚያስችል ሁናቴዎችን ላለመፍጠር ባደባባይ ከመናገር ይልቅ ከጀራባህ የሚያካሂዱት ሴራ ፈጦ የወጣበት ሁኔታ ይስተዋላል።

ስማኝ ህዝቡ ስማኝ ሀገሩ!

በሌላ በኩል የግንዛቤ ግድፈት ትግሉ ላይ ከሚያሳድረው ጫን ባሻገር ትውልድህ ራስ ወዳድነት ንፉግነት ምቀኝነትና ህብረት ማጣት ፍርሃትና ሃሞተቢስነት ከምንግዜውም የበለጠ እንዲቆራኙት በመደረጉ ከ1650 ኪሎሜትር በላይ የሀገርህ ግዛት ለሱዳን ሲሰጥ ተመልካች ሆንክ፣ከ 2.4 ሚሊዎን በላይ የዐማራ ህዝብ ከቆጠራ ጠፋ ሲባል በፌዝ አለፍክ፣ ከምስራቅ ከደቡብና ከምዕራብ ኢትዮጵያ ከመኖሪያ ቀያቸው ዐማሮች በመሆናቸው ብቻ ንብረታቸው ተዘርፎ የተባረሩት ወገኖችህ ብቻቸውን በጸሃይ በዝናብና ብርድ ተቆራመደው በረሃብ አለንጋ ተገርፈው በየመንገዱ ወድቀው ቀሩ፣ የወልቃይት ጠገዴ ወገንህ ብቻውን በተናጥል ዳሸቀ፣ ገዳማትና ታሪካዊ ቅርሶችህ ሲዘረፉና ሲወድሙ፣ የሃይማኖት መረዎችና ባህታውያን ሲታሰሩና ሲገደሉ አንተም ሆንክ እንመራሃለን የሚሉህ ድርጅቶችህና መሪዋችህ በፍርሃት ዝምታ ተውጥው ቀሩ።

ስማኝ ህዝቡ ስማኝ ሀገሩ!

ላንተ ደህንነት ካንተ ከችግሩ ገፈት ቀማሽ ወዲያ መፍትሄ አፈላላጊ ሊኖር እንደማይችል ያሳለፍካቸው 21 የሰቆቃ እና የመከራ ዓመታት ዋቢ ናቸው ። ያንተ በግንዛቤና በዕውቀት ላይ መሰረት ያረገ መተባበርና መደራጀት ለነገ በይደር የሚተው ሳይሆን ትናንት መሆን የነበረበት መራራ ሃቅ ነው። ዘላለም ባርያ ከምትሆን በመስዋዕትነት አንድ ቀን በነጻነት መኖርን የመሰለ ክቡር ህይወት የለም። ዘላለም ቀስ በቀስ በስቃይ ሞትን ከመቀበል ይልቅ በቆራጥነት ታገል ታሽንፋለህ! ያለያ ባርያ ትሆናለህ! ለልጅ ልጆችህም ባርነትን ታወርሳለህ።

E-Mail Address:- amaraunionmoresh@gmail.com

ዛሬ ተጠንቀቅ አማራ – በPDF

Advertisements
Categories: Articles