Home > TPLF woyane > ሃይለማርያም ደሳለኝ እንደ ቴሌቭዥን በRemote Control የሚሰራ ጊዜያዊ ጠ/ሚ/ር ሆነ

ሃይለማርያም ደሳለኝ እንደ ቴሌቭዥን በRemote Control የሚሰራ ጊዜያዊ ጠ/ሚ/ር ሆነ

August 21, 2012

ሃይለማርያም ደሳለኝ በብርሃኔ ገብረክርስቶስናእና በስዩም መስፍን የሚንቀሳቀሱ ባለሪሞት ኮንትሮሉ ጊዜያዊ ጠቅላይ ሚኒስተር ሆነው ተሾሙ። በሕወሓት ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ድንጋጤ ከመግባቱም በላይ የስልጣን ሽኩቻውም እያየለ ነው የሚሉ መረጃዎች እየወጡ ነው። ኢትዮጵያም በታሪኳ በሶስት ቦታ ሪሞት ኮንትሮል ሆኖ የሚያገለግል ሰው አግኝታለች።

ከአንድ ቀን በፊት የአቶ መለስ ዜናዊ አስከሬን፤ ከውጭ አገር እንዲገባ ተደርጎ በቦሌ ተርሚናል የሬሳ ማቀዝቀዣ ክፍል ውስጥ ተቀምጦ እንደቆየ የኢትዮጵያ ሚድያ መድረክ EMF አጋለጠ። ኢቲቪ አቶ መለስ የሞቱት ትናንት እንደሆነ አድርጎ መዘገቡ ዳግመኛ ውሸት መሆኑንና መለስ ከሞቱ መቆየታቸውን በርካቶች እየገለጹ ይገኛሉ።

እንደ ኢትዮጵያ ሚድያ መድረክ ዘገባ የመለስ ዜናዊ ዜና እረፍት ከተሰማ በኋላ፤ ልጆቻቸውን በመለስ አስተዳደር የተነጠቁ ወላጆች፤ ፍትህ አጥተው በእስር እና በስደት ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ደስታቸውን ሲገልጹ፤ ቀኑ የጨለመባቸው የኢህአዴግ ወገኖች ደግሞ ሆድ ብሷቸው ሲያለቅሱ ውለዋል።

በአሁኑ ወቅት. የመለስ ዜናዊን ቦታ ተክተው እንዲሰሩ የተደረጉት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ሲሆኑ፤ የጠቅላይ ሚንስትርነቱ ቦታ ወደ ሌላ ብሄር መሄዱ በዘረኝነት አጥር ውስጥ የሚገኙትን በተለይም፤ የህወሃት ከፍተኛ አመራር እና የጦር አዛዦችን ያስኮረፈ ይመስላል። በአሁኑ ወቅት ጄነራል የሳሞራ የኑስን ህመም ተከትሎ የኢትዮጵያ የጦር ሰራዊት በመንታ መንገድ ላይ ይገኛል። በአጠቃላይ የአየር ኃይል እና የምድር ጦር ሰራዊቱ ከአዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ መስመር ውጪ በህወሃት ከፍተኛ የጦር መኮንኖችም አመራር ስር መውደቁ ይታወቃል።

አቶ ሃይለማርያም ለስሙ በዚህ ስልጣን ላይ ይቀመጡ እንጂ የሚያንቀሳቅሷቸው አቶ ስዩም መስፍን እና ብርሃኔ ገብረክርስቶስ እንደሆኑ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ጠቁመዋል።

የአባ ጳውሎስ የቀብር ስነ ስር ዓት የፊታችን ሃሙስ በቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የሚከናወን ሲሆን፤ የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር የቀብር ስነ ስር ዓት የት እና መቼ እንደሚከናወን አልታወቀም።

Sorce: www.zehabesha.com

Advertisements
Categories: TPLF woyane
%d bloggers like this: