Home > TPLF woyane > ጋለሞታ አዜብ መስፍን በስሟ ያለ ማንኛውም ገንዘብና ንብረት እንዳይንቀሳቀስ መመሪያ ተላለፈ – (*_*)

ጋለሞታ አዜብ መስፍን በስሟ ያለ ማንኛውም ገንዘብና ንብረት እንዳይንቀሳቀስ መመሪያ ተላለፈ – (*_*)

August 21, 2012

(ዳዊት ዋስይሁን/ኢትዮቼንጅ ብሎግ)፦ ከአቶ መለስ መሰወር በኹአላ እየተፍረከረከ የመጣው የህወሐት ጠባብ ቡድን ከተወሰኑ ቀናቶች ጀምሮ ከመሃከላቸው የሆነ አስፈሪ ነገር እየተፈጸመ እንዳለ እየታየ ነው።

ይህም ክስተት ነባር እና ታማኝ ተብለው በድርጅቱ ተፈርጀው የነበሩ ካድሬዎችንና አባላትን ይበላ ጀምሯል፤ ይህ የሚደንቅ አይደለም ምክንያቱም አብዮት ወልዳ ያሳደገቻቸውን ልጆች እንደምትበላ የታሪክ እውነታ ስለሆነ ይህንን ደግሞ ለመስዋእት የቀረቡ የህውሃት ካድሬዎች ሊገነዘቡት ይጋባል።

የአቶ መለስ ጥላ ሰብስቦ ይዟቸው የነበር አቅመ ደካማና ልፍስፍስ ቱባ ባለስልጣናት ሁሉ ጥላው ሲነሳ የሚሆኑት ግራ ገብቶአቸው በቀን ቅዠት ውስጥ ነው ያሉት። በደረሰን ትክክለኛ መረጃ መሰረት ከፍተኛ የህወሐት ባለስልጣናት ባለፈውና በአሁኑ ሳምንት የደቡብ አፍሪካንና የሳውዲ ሆስፒታሎችን እያጥለቀለቁ ሲሆን። የበሽታቸውም ዋናው ምንጭ ተደርጎ የተነገራቸው በስርአቱ መዋዠቅ የተፈጠረ የኧምሮ መረበሽ እና ጭንቀት ነው።

የዚህ የአለመረጋጋት በሽታ ተለጣፊ ተብዬዎችንም እያጠቃቸው እንዳለ እየታየ ሲሆን ለማስረጃ ብአዴን ሰሞኑን በመተራመስና በመበጥበጥ አሳልፏል። ከነዚህ ተለጣፊዎች መሃል ትንሽ መረጋጋት የሚታይበት ኦህዴድ እንደሆነ ሲነገር። የዚህ መረጋጋት ምንጭ ደግሞ የተፈጠረውን መደነጋገር ተጠቅሞ የስልጣን ማማውን ለመያዝ ውስጥ ውስጡን እየሰሩና እየዶለቱ እንዳለ ከአቶ ኩማ ደመቅሳ አካባቢ የሚከናወነው ህቡእ ስራ ይህንን ያረጋግጣል በዚህ ጨዋታና ደባ ውስጥ አባ ዱላ ገመዳ ከውጭ ሆነው የሚሆነውን እየተመለከቱ እየቀመሩ ሲሆን የሂደቱ ውጤት አትራፊ ከሆነ በተካኑት የዘረፋ ቴክኒክ የድል አጥቢያ አርበኛ ለመሆን ነገር ግን መስዋእት የሚያስከፍል ከሆነ የለሁበትም ለማለት አቆብቁበው እንዳሉ ይታያል።

በማያያዝ የአቶ መለስ ዜናዊ ሚስት ወ\ሮ አዜብ መስፍን ደብዛቸው ከጠፋ ይኸው አንድ ወር ሆናቸው ይህ አጠፋፋቸው ደግሞ ከኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ከቤተሰባቸውም ጭምር ነው ይህንንም ተከትሎ ወ\ሮዋ ይስሩበት እና ያስተዳድሩት የነበረውን ኤፈርት እንዲለቁ መደረጉን እና ቢሮአቸው መታሸጉን እንዲሁም በፊርማቸው ይንቀሳቀሱ የነበሩ የኤድስ ፈንድ እንዲሁም የሴቶች ኮር ገንዘብ የትም ቦታ ሆነው እንዳያንቀሳቅሱ መደረጋቸውንና ለግዜው ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ማንኛውም በስማቸው ያለ ንብረት ለማንኛውም አካል አሳልፈው እንዳይሰጡ እገዳ እንደተጣለባቸው መረጃዎቻችን አረጋግጠዋል። የሴትየዋ መሰወር ቤተሰቦቻቸውን በጣም እንዳሳሰበ ቤተሰቦቻቸው በመረበሽ ይገልጻሉ።

በአሁን ሰአት ወ\ሮ አዜብ አገር ውስጥ እንዳልሆኑ ሲገለጽ ነገር ግን ባሉበት ቦታ ቢሆንም የሚያረጉትን እንቅስቃሴ በደህንነት ክትትል ስር እንዲሆን መመሪያ ተላልፏል። እንደውም በአንዳንድ የህውሓት ነባርና ታማኝ አባላት ዘንድ ሴትየዋም ሆነ ባላቸው ለህክምና እየተባለ በ100ሺዎች ዶላር የሚቆጠር የድርጅቱንና የሃገሪቱን ገንዘብ ካለተጠያቂነት ሲያጠፉ ማን ፈቃድ ሰጣቸው የሚል ጥያቄዎችንም በመፍጠሩ ሳይሆን አይቀርም ሴትየዋ በስማቸው ይንቀሳቀሱ የነበሩ ገንዘቦች ሁሉ እንዲረጉ የታዘዙት።

Source: www.zehabesha.com

Advertisements
Categories: TPLF woyane
%d bloggers like this: