Home > Articles > እድሜ እና መጽሃፍ ያላስተማረው ሽማግሌው ስብሃት ነጋ

እድሜ እና መጽሃፍ ያላስተማረው ሽማግሌው ስብሃት ነጋ

October 26, 2012

By: Asress M.

ከሰማንያ ሚሊየን ኢትዮጵያዊ ውስጥ መቸም እንደ ስብሃት ነጋ ያልሰለጠነ እና ከዘመኑ ጋር የማይራመድ ሰው ይኖራል ብየ አልገምትም:: ባጠቃላይ በኢህአዴግ ሰዎች አቋም የለሽነት አምባገነንነት እና ጠባብነት ላይ ቅሬታ ቢኖረኝም የአቶ ስብሃት ነጋን የለት ተለት የጥላቻ እና የመሃይምነት የቁልቁሊት ጉዞ ሳይ ግን እጅግ ይደንቀኛል:: አቶ ስብሃት ነጋ ወደ ትግል ሲገቡ የብሄር ጭቆና አለ ትግራይ ተጨቁኗል ያንድ ብሄር የበላይነት ሰፍኗል ስለዚህ ነጻነታችን እንፈልጋለን በማለት ነበር:: ካስራ ሰባት አመት ጦርነት በኋላ የትግራይን ህዝብ ነጻ አውጥተናል አሉ:: መልካም እንኳን ወገናችን የሆነው የትግራይ ህዝብ ነጻ ወጣ:: እኔ በበኩሌ ማንም ተጨቁኖ እንዲኖር አልፈልግም:: ነገር ግን የአቶ ስብሃት መሃይምነት የሚገርመው እራሳችን ነጻ አውጥተናል ካሉ በኋላ ሌላውን ብሄር ለማንቋሸሽ ለማዋረድ እና ለመጨቆን የሚያደርጉት ሴራ ነው:: ከአቶ ስብሃትና ከመሰሎቹ የመሃይምነት ድፍረት ንግግሮች ውስጥ ጥቂቶቹን ለመግለጽ ያህል፤

1. “አማራውን እንዳይነሳ አድርገን ቀብረነዋል”

2. “አማራው እና የኦርቶዶክስ ሃይማኖት የዲሞክራሲ ጠላቶች ናቸው”

3. “መሬት እንዲሸጥ ካደረግን አማሮች ገዝተው ይጨርሱታል”

4. “ነፍጠኞች ናቸው በሏቸው ጊዜው የናንተ ነው አንገታቸውን አስደፏቸው”

እነ አቶ ስብሃት ይህን ሁሉ የመሃይምነት ድፍረታቸውን ሲያሳዩ እስከ አሁን ድረስ ባዶ እግሩን የሚሄደውን የአማራው ህዝብ እና ከዚህ በፊት በስሙ ይነግዱ የነበሩ ጥቂት የገዥ መደቦች ምን አገናኛቸው ብለው አለማሰባቸ ይደንቃል? እውነት ለመናገር እነ አቶ ስብሃት የብሄር ብሄረሰብ ጥቅም አስመስለው ለከፋፍለህ ግዛው ዘዴያቸው እና የራሳቸውን ገዥ መደብ ለመፍጠር ሲራወጡ ተራው ዜጋ አማራ አማራነቱን እንኳ አያውቅም ነበር። ጎንደሬ ወሎየ ጎጃሜ ሸዋየ እየተባባለ ከመኖር በስተቀር የጎሳ ስሜት አልነበረውም። ለዚህም ነው ከትግሬው ከጉራጌው ከኦሮሞው ከወላይታው እና ከሌላውጋር ተደበላልቆ የኖረው። የነ አቶ ስብሃቱ ገዥ መደብ ግን ካገር ውስጥ እስከ አገር ውጭ በጎሳ ተደራጅቶ 50 ዓመት ሌላውን እረግጨ እገዛለሁ እያለን ይገኛል። ይህ አማራውን በማንቋሸሽ እና ማዋረድ የተጀመረው የእነ አቶ ስብሃት የመሃይምነት ድፍረት እየተለጠጠ ሄዶ አሁን ለሌላውም ጎሳ እንዲሁም ባጠቃላይ የኢትዮጵያን ህዝብ ወደ ማዋረድ መናቅና ማንቋሸሸ ተሸጋግሯል ይህንን ለመረዳት የሚከተለውን የሰሞኑ የአቶ ስብሃት ንግግር መመልከት በቂ ነው፡፡

“የኢትዮጵያ ህዝብ ለዲሞክራሲ ብቁ አይደለም” … መቸም እንዲህ ብሎ ህዝብን መናቅ እና ይህን ንግግር መናገር የመጨረሻው የመሃይምነት ድፍረትን ማሳየት ወይም በአፉ የሚሸና ከፉ አውሬን መምሰል ነው፡፡

ይህ ሌሎች ብሄሮችን ለማንቋሸሽ እና ቅስም ለመስበር የሚደረገው ሙከራ ግን መቸም ቢሆን እንደማይሳካላቸው አቶ ስብሃት ሊያውቁት ይገባል:: የኋላ ኋላም እራሳቸውን ለውርደት እንደሚያበቃቸው አልጠራጠርም:: ለዚህም ማን ይነካናል ባዮቹን እነ ሳዳምን ጋዳፊን ቤን አሊን ሙባረክን እንዲሁም አሁን በጭንቀት ላይ ያለውን የሶርያው አሳድን መመልከት ይጠቅማል፡፡ በቅርቡም ደቀ መዝሙራቸው አቶ መለስ ዜናዊ ያደንቁኛል ብለው በሚያስቧቸው የዓለም መሪዎች ፊት ምናልባትም “እንዳይነሳ አድርገን ቀብረነዋል“ ከተባለው ህዝብ በተገኘ አንድ ግለሰብ እንደዚያ ተዋርደው እና አንገት ደፍተው በመጨረሻም ለሞት መብቃት ተመለክተው አቶ ስብሃት እንዲማሩና ከአንደበታቸው የሚወጣውን በካይ ንግግራቸውን እንዲገቱ እንምከራቸው::

source: www.zehabesha.com

Advertisements
Categories: Articles
%d bloggers like this: