Home > Articles > ትግራይ በስብሰባ ተጨንቃ ከረመች

ትግራይ በስብሰባ ተጨንቃ ከረመች

November 7, 2012

ዘ.ሙ.

…በ1983 ዓ.ም ደርግን ለመጣል በተቃረበበትና የኤርትራ ሪፈረንደም እንዴት ይፈፀም በሚለው ርዕስ ጉዳይ ላይ ካካሄደው የሶስት ወር ህዝባዊ ስብሰባ ቀጥሎ በግዙፍነቱ የሚጠቀስ ነው።

[የትግራይ ህዝብ በኤርትራ ሪፍረንደም ጉዳይ ላይ ተወያይቶ ኤርትራ እንድትገነጠል ተስማማቶ ነበር ማለት ነው።]

ህዝባዊ ወያኔ ኧርነት ትግራይ (ህወሓት) ከተመሰረተ በኋላ ከተደረጉ ሕዝባዊ ሰብሰባ ግዙፍ ነው የተባለበት ስብሰባ በመላ ትግራይ ሲካሄድ መሰንበቱን የክልሉ ምንጮቻችን አመለከቱ።

የስብሰባው ዋና ትኩረት የመለስን ራዕይ “ኧንፃት” በማስቀጠል ላይ ያተኮረ ሲሆን በቅድሚያ በከፍተኛ አመራሮች ሲካሄድ የሰነበተው ስብሰባው በየደረጃው ላሉ መዋቅሮች እንዲወርድ ተደርጓል።

የክልሉ የመረጃ ምንጮች ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፁት በትግራይ በተካሄደው በዚሁ ስብሰባ ላይ ከአንድ ሚሊዮን ያላነሰ ሕዝብ ሳይከፈል እንደልቀረም የጠቆሙ ሲሆን በስብሰባው ላይ ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 60 የሚሆኑ የህብረተሰቡ ክፍሎች ተካፍለዋል።

ስብሰባው በሴቶችና በወንዶች እንዲሁም በባለሀብቶች ተለይቶ መካሄዱን የገለፁት ምንጮች በስብሰባው ለተካፈሉ በቀን እስከ 35 ብር አበል እንደተከፈለም ምንጮች ጠቁመዋል።

በክልሉ ቀደም ሲል ከነበረው የአንድ ለአምስት አደረጃጀት በተጨማሪ አዳዲስ የህዝብ አደረጃጀቶች ተግባራዊ እንደሚደረጉም ተመልክቷል። በዚህም መሰረት አንድ ለአምስት አደረጃጀት (አንድ ህዋስን) በስድስት ህዋስ በማጣመር ስድስቱን ህዋሳት በአንድ ላይ የሚጠረንፍ አራት ሰዎችን ተዋቅረዋል። በዚህም መሰረት 4ለ30 የተባለ አዲስ አደረጃጀት መፈጠሩም ተገልጿል።

ከዚህ አዲሱ አደረጃጀት በተጨማሪ በገጠርና በከተማ በአባወራ ደረጃ አንድ አባወራ በስሩ አስር አባወራዎችን የሚያደራጅ ሲሆን አባወራና እማወራ ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር በመሆን ጭምር ልጆቻቸውን የሚጠረንፉበት (የሚያሰባስቡበት) አደረጃጀት ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል።

በክለሉ ይበልጥ ተግባራዊ እንዲደረግ ከታቀደው ፖለቲካዊ አደረጃጀት በተጨማሪ በተያዘው አመት 750 ሺህ አርሶ አደሮች በመስኖ እንዲያለሙ፣ በክልሉ 50 በመቶ የሚሆነው መሬት እንዲታረስና ከግብርና ምርት በተጨማሪ ከ40 እስከ 50 ሚሊዮን ኩንታል አትክልትና ፍራፍሬ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዷል። ለዚህ እቅድ ተግባራዊነትም ሁሉም አርሶ አደር ማዳበሪያ እንዲጠቀም መመሪያ መውረዱም ተመልክቷል።

ከአቶ መለስ ህልፈት በኋላ ለአንድ ወር በየደረጃው ሲካሄድ የቆየው ስልጠና የተሳተፉ በሙሉ የህወሐት አባል እንደሆኑ ሁሉም የተደራጁ ህዋሳት በመካከላቸው ያለውን ግንኙነት በማጠናከር ምንም አይነት ክፍተት ሳይፈጥሩ ታላቁ መሪ ያስቀመጡትን ራዕይ እንዲያሳኩ፣ ለራዕዩ እንቅፋት የሚሆኑትንም እንዲታገሉ የሚል መመሪያ መውረዱ የተገለፀ ሲሆን ድርጅቱ በ1983 ዓ.ም ደርግን ለመጣል በተቃረበበትና የኤርትራ ሪፈረንደም እንዴት ይፈፀም በሚለው ርዕስ ጉዳይ ላይ ካካሄደው የሶስት ወር ህዝባዊ ስብሰባ ቀጥሎ በግዙፍነቱ የሚጠቀስ ነው ተብሏል። ይህ ስብሰባ በዛን ጊዜ ተደርጎ ከነበረው ስብሰባ የሚለየው በዕድሜ አነስተኛ የሆኑ ወጣቶችን ከማሳተፉም በላይ በቤተሰብ ደረጃ መካሄዱ ነው ተብሏል።

ምንጭ፡ ሰ.ጋ

—————————-

ወያኔ በ3 ቀን በስብሰባው በተካፈሉ 1 ሚልዮን የሚሆኑ የትግራይ ተወላጆች በቀን 35 ብር የውሎ አበል እየከፋ ያካሄደው ስብሰባ በጠቅላላቅ ሌላ ለላ ወጭወችን ሳይጨምር

1,000,000 * 35 * 3 = 105 ሚልዮን ብር ነው የፈጀው ማለት ነው።

Advertisements
Categories: Articles