Home > News > አሻንጉሊቱ ኃይለማርያም ደሳለኝ 3 ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች በወያኔ ተመደበለት

አሻንጉሊቱ ኃይለማርያም ደሳለኝ 3 ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች በወያኔ ተመደበለት

November 29, 2012

(ዘ-ሐበሻ) ከዚህ ቀደም አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ወደ ስልጣን ከመምጣታቸው አስቀድሞ ኢትዮጵያ 3 ጠ/ሚ/ሮች እንደሚኖራት በዘ-ሐበሻ ድረ ገጽ ተዘግቦ ነበር። ዛሬ ኃይለማርያም ደሳለኝ በፓርላማ ቀርበው 2 ተጨማሪ ምክትል ጠ/ሚ/ሮችን እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን ቦታ ለሕወሓት በማስረከብ አስጸድቀዋል። ሃገሪቱን በጋራ እንመራታለን ያሉትን በተግባርም አሳይተዋል። ዛሬ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የቀረበውን የካቢኔ አባላት ሹመት ባጸደቀበት ወቅት እንደተገለጸው የካቢኔ ጉዳዮች በማህበራዊ፣ በመልካም አስተዳደር እና በፋይናንስና ኢኮኖሚ ዘርፍ ተከፋፍሎ ሹመቱ መካሄዱን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ አስታውቀዋል።

በዚህም መሰረት የኦህዴዱ አቶ ሙክታር ከድር በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ ፥ የመልካም አስተዳደርና ሪፎርም ክላስተር አስተባባሪና የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር፤

የሕወሓቱ ምክትል ሊቀመንበርና ሃገሪቱን ነጻ ሚድያ እንዳታገኝ ኢትነርኔትን ጭምር በማፈን የታወቀኡት ዶክተር ደብረ ፅዮን ገብረ ሚካኤል በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ ፥ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር፤

የሕወሓቱ ዶክተር ቴዎድሮስ አድኃኖም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፤

ተጠባባቂ የንግድ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ከበደ ጫኔ የንግድ ሚኒስትር፤

የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዲኤታ የነበሩት ዶክተር ከሰተብርሃን አድማሱ ደግሞ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር፤ በመሆን ከተሾሙ በኋላ አዲሶቹ ተሿሚዎች በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አማካኝነት ቃለ መሃላ ሲፈጽሙ ታይተዋል።

ኦህዴድ ቁልፍ ስልጣን ቦታ አጥቷል በሚል ከፍተኛ የሆነው ብጥብጥ ውስጥ ገብቶ የነበረ ቢሆንም የአቶ ሙክታር ከድር በምክትል ጠ/ሚ/ር ማዕረግ መሾም ጉዳዩን ለማብረድ ቢሆንም አሁንም ቁልፍ ስልጣኖች በሕወሓት ሥር መቀመጣቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ምንም የተፈጠረ ለውጥ የለም; አድሏዊው ሹመት አሁንም እንዳለ ነው የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች በርካታ ናቸው።

source: Zehabesha.com

Advertisements
Categories: News
%d bloggers like this: