Home > News > በዛሬው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ አስገራሚ ነገሮች ተሰሙ | Zehabesha com

በዛሬው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ አስገራሚ ነገሮች ተሰሙ | Zehabesha com

January 15, 2013

Tribalist Tigre(ዘ-ሐበሻ) በአዲስ አበባ አስቸኳይ ስብሰባ የተቀመጠው የሃገር ቤቱ ሲኖዶስ በዛሬው ውሎው የመንግስት ደጋፊ የሆኑ ጳጳሳት ፍላጎት በአሸናፊነት ጎልቶ በመውጣት ላይ እንዳለ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ከስፍራው ዘገቡ። እንደምንጮቹ ገለጻ ከትግራይ የመጡት ጳጳሳት “አቡነ መርቆርዮስ ወደ ኢትዮጵያ የሚመለሱ ከሆነ ትግራይ የራሷን ፓትርያርክ በመሾም በእርሱ እንመራለን፤ ቤተክርስቲያንንም እንከፍላለን” የሚል አቋማቸውን ማሳየታቸውን የዘ-ሐበሻ ታማኝ ምንጮች ዘግበዋል።

ዛሬ በአዲስ አበባ የተጀመረውና ምናልባት ነገ ሊጠናቀቅ አልያም ሊቀጥል ይችላል የተባለው ይኸው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ከትግራይ ተወላጅ የሆኑት 18ቱም ጳጳሳት መገኘታቸው የታወቀ ሲሆን “አዲስ ፓትርያርክ ይመረጥ የሚለውን አቋማቸውን” አጠናቅረውበት ከመቀጠላቸውም በተጨማሪ ሌሎች ፓትርያርክ እንዳይመረጥ የሚፈልጉ አባቶች ከቅዳሜ ጀምሮ በድህነነት ኃይሎች እንግልት ውስጥ በመግባት ሃሳባቸውን እንዲቀይሩ በመደረግ ላይ እንዳሉ እነዚሁ የዘ-ሐበሻ ምንጮች አጋልጠዋል።

በተለይም የመንግስት ተወካይ ሆነው የቀረቡት አቶ አባይ ጸሐዬ በግልጽ አዲስ ፓትርያርክ መሾሙን ለማይደግፉ አባቶች “አቡነ መርቆርዮስ ይመለሱ ከምትሉ ለምን መንግስቱ ኃይለማርያም ይምጣ አትሉም?” በማለት እንደተናገሯቸውና እንዳስፈራሯቸው ያረጋገጡት የዘ-ሐበሻ ምንጮች በተለይ ከትግራይ የመጡት ጳጳስት አቡነ ሳሙኤል (ፎቶ)ና አቡነ ጎርጎርዮስ የአቡነ መርቆርዮስን መመለስም ሆነ ፓትርያርክ እንዳይሾም የሚጠይቁትን አባቶች ስም ዝርዝር ለመንግስት በመስጠት በደህንነት ኃይሎች አቋማቸውን እንዲቀይሩ ትልቅ ሥራ እየሰሩ መሆኑም ተጋልጧል።

በዛሬው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ በተለይ አቡነ መርቆርዮስ የሚመለሱ ከሆነ ትግራይ የራሷን ፓትርያርክ ትመርጣለች የሚል የማስፈራሪያና ቤተክርስቲያንን አደጋ ላይ የሚጥል አነጋገር መሠማቱ ብዙ የ ዕምነቱን ተከታዮችን አስደንግጧል። በአጠቃላይ በዛሬው የሲኖዶስ ስብሰባ የመንግስት ደጋፊ የሆኑ ጳጳሳት በአሸናፊነት እየመሩ ነው። ስብሰባው ነገ ይቀጥላል። በስብሰባው ውስጥ ያሉት የዘ-ሐበሻ ምንጮች መረጃውን እንዳደረሱን ለአንባቢዎቻችን ያለውን ነገር እናሳውቃለን።

Source: Zehabesha.com

Advertisements
Categories: News
%d bloggers like this: