Home > TPLF woyane > ወያኔ ለ34 ኮለኔሎችና ለ3 ብ/ጄነራሎች የጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ [ጠቅላይ ሚኒስትሩ] በሌለበት ከፍተኛ ማዕረግ ሰጠ።

ወያኔ ለ34 ኮለኔሎችና ለ3 ብ/ጄነራሎች የጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ [ጠቅላይ ሚኒስትሩ] በሌለበት ከፍተኛ ማዕረግ ሰጠ።

September 12, 2012

ህገ መንግስቱ  ረቂቅ አዋጅ መሰረት የጄነራሎችን በእጩነት ማቅረብ የሚቻለው ከመከላከያ ሚንስትር ውስጥ ከተቋቋመው ኮሚቴ ለጠቅላይ ሚንስትሩ በማቅረብ ሲሆን ጠቅላይ ሚንስትሩ ደግሞ አስፈላጊውን ጥናታዊ ከተመለከቱ በኋላ ለሃገሪቱ አስተዳደራዊ መንግስት ወይንም ፕረዚዳንት እጩዎቻቸውን በማቅረብ የሹም ሽር የሚከናወነው  በሃገሪቱ ርእሰ ብሄር ከሆኑት ፕረዚዳንት  የሚደረግ ህግ የነበራት ሃገር  የነበረችው ኢትዮጵያ እስከ 1993 አም. በዚህ አስተዳደራዊ ስርአት ትተዳደር ነበር ።በ1993 አ.ም በተፈጠረው የህወሃት ክፍፍል ጠ/ሚንስትሩ በፓርቲው መሃከል ጣልቃ በመግባት ለራሳቸው በሚመቻቸው መልኩ አገሪቱን ለማሽከርከር እና የሚፈልጉትን ሰው በሚፈልጉት ቦታ ለማስቀመጥ  2 ጄነራሎችን አባረሩ እነዚህም  ሜ/ጀነራል ጻድቃን ገ/ትንሳይ እና አበበ ተ/ክለሃይማኖት (ጆቤ) ሲሆኑ ፣እነዚህን ጀነራሎች ካባረሩ በኋላም  ከሃገሪቱ ርእሰ ብሄር  ከነበሩት ፕረዚዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ጋር በተደረገው ውይይት እና በተፈጠረው አለመግባባት ጠ/ሚንስትሩ ስህተታቸውን  ከማረም  ይልቅ የሃገሪቱን ህገ መንግስት እንደ ገና የጠቅላይ እዙ እና ሹም ሽር በእሳቸው (በጠ/ሚንስትሩ )እጅ እንዲዞር አደረጉ።

ያገሪቱ ፕረዚደንት ማባረር እና ስልጣን ሰጥቶ መሾም ሲገባው  የቀድሞውን ፕረዚዳንት ዶ/ነጋሶ ጊዳዳ ይህንን ባለማድረጋቸው  ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር በመነጋገርጠቅላይ ሚንስትሩ ህግ በመጣሳቸው እስከ መጋጨት ደርሰው  እስከ ስልጣን መልቀቂያ ድረስ ማቅረባቸው የሚታወስ ነው ። ሆኖም ዛሬም ጠ/ሚንስትሩ በህይወት በሌሉበት እና እንደገና የቀድሞው ጠ/ሚንስትር ሽረውት በእጃቸው እንዲሆን ያደርጉት የሹም ሽር ሂደት ዛሬ ደግሞ በሃገሪቱ ፕረዚደንት ሊከናወን ችሏል ።ተጠሪነቱም በጠቅላይ ሚንስትሩ በኩል የነበረው የመከላከያ ሚንስትር ኮሚቴ አባላትም ተግባራቸው ምን ደረጃ እንደድረሰ ሳይታወቅ የህገመንግስቱ መሻር እና የስልጣን መበራከት ጀምሯል:: የሃገሪቱ ህገ መንግስት የተቀመጠው ለይስሙላ ይሆን እንዴ?ለምንስ እንደገና የሃገሪቱን ህገ መንግስት በመጣስ ጀነራሎችን የማእረግ ሽልማት ሊሰጣቸው ቻለ ?በአገሪቱ ህገመንግስት መሰረት 34 ኮሎኔሎች በብራጋዴር ጄነራል ማዕረግ ፣ ሶስት ብራጋዴር ጄነራሎች ደግሞ በሜጀር ጄነራል ማዕረግ ተሹመዋል፡፡ አብዛኞቹም የትግራይ ተወላጆች ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ ከሁለት ወገን የዘር ሃረግ ያላቸው ናቸው ፣ከእነዚያም ውስጥ የትግራይ ተወላጆች እንደሚበዙ ከሪፖርቱ ተገልጿል፡፡

በተሰጠው ከፍተኛ ወታደራዊ ሹመት መሰረት ብራጋዴር ጄነራል ሆነው የተሾሙት ብራጋዴር ጄነራል ያይኔ ስዩም፣ብራጋዴር ጄነራል አታክልቲ በርሄ ፣ብራጋዴር ጄነራል ፍስሃ በየነ፣ ብራጋዴር ጄነራል ጉዕሽ ፅጌ ፣ ብራጋዴር ጄነራል ገብረኪዳን ገብረማሪያም፣ብራጋዴር ጄነራል ማዕሾ ሃጎስ፣ብራጋዴር ጄነራል ገብሩ ገብረሚካኤል፣ብራጋዴር ጄነራል ማሸሻ ገብረሚካኤል፣ ብራጋዴር ጄነራል አብረሃ አረጋይ፣ ብራጋዴር ጄነራል ደግፊ ቢዲ ናቸው፡፡

እንዲሁም ብራጋዴር ጄነራል አስካለ ብርሃነ፣ ብራጋዴር ጄነራል ሀለፎም እጅጉ፣ ብራጋዴር ጄነራል አብርሃ ተስፋዪ፣ ብራጋዴር ጄነራል ሙሉ ግርማይ፣ብራጋዴር ጄነራል ወልደ ገብርኤል ባቢ፣ብራጋዴር ጄነራል ፍሰሃ ኪዳነ ማሪያም፣ብራጋዴር ጄነራል አሰፋ ገብሩ፣ብራጋዴር ጄነራል የማነ ሙሉ፣ብራጋዴር ጄነራል ገብረመድህን ፍቃዱ፣ብራጋዴር ጄነራል ታረቀኝ ካሳሁን፣ብራጋዴር ጄነራል አስራት ዶኖይሮ፣ብራጋዴር ጄነራል ጥጋቡ ይልማ የማዕረግ ዕድገቱ ከተሰጣቸው መካከል ናቸው፡፡

በተመሳሳይ እንዲሁ ብራጋዴር ጄነራል ዘውዱ በላይ፣ብራጋዴር ጄነራል ኩምሳ ሻንቆ፣ብራጋዴር ጄነራል አጫሉ ሸለመ፣ ብራጋዴር ጄነራል ሹማ አብደታ፣ብራጋዴር ጄነራል ድሪባ መኮንን፣ብራጋዴር ጄነራል ደስታ አብቺ፣ብራጋዴር ጄነራል አቤል አየለ፣ብራጋዴር ጄነራል ይመር መኮንን፣ብራጋዴር ጄነራል ከድር አራርሳ፣ብራጋዴር ጄነራል ይብራህ ዘሪሁን፣ ብራጋዴር ጄነራል ኩመራ ነጋሪ፣ብራጋዴር ጄነራል ዱባለ አብዲ ናቸው፡፡

ሜጀር ጄነራል ሆነው የተሾሙት ደግሞ ሜጀር ጄነራል መሐሪ ዘውዴ፣ ሜጀር ጄነራል ሐሰን ኢብራሂምና ሜጀር ጄነራል መሰለ በለጠ መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል

source:www.maledatimes.com

ወያኔ ለ34 ኮለኔሎችና ለ3 ብ/ጄነራሎች ከፍተኛ ማዕረግ ሰጠ፤ (የሹመቱ የብሔር ተዋጽኦን ይዘናል)

የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት ፕሬዚዳንቱ ወታደራዊ ሹመት ይሰጣሉ ይላል። ሆኖም ግን በሞተ ጠቅላይ ሚኒስትር እስካሁን እየተመራን በምንገኝበት በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ህገመንግስት መሰረት 34 ኮሎኔሎች በብራጋዴር ጄነራል ማዕረግ ፣ ሶስት ብራጋዴር ጄነራሎች ደግሞ በሜጀር ጄነራል ማዕረግ ተሹመዋል፡፡ በሹመቱ ላይ የተሰተዋወለው የብሔር ተዋጽኦ አሁንም እጅግ አነጋጋሪ እንደሆነ ነው።

በተሰጠው ከፍተኛ ወታደራዊ ሹመት መሰረት

ብራጋዴር ጄነራል ሆነው የተሾሙት:-

ተ/ቁ
ማ ዕረግ
ስም
ብሄር
1 ብ/ጄ ያይኔ ስዩም ብሔር ትግሬ
2 ብ/ጄ አታክልቲ በርሄ ብሔር ትግሬ
3 ብ/ጄ ፍስሃ በየነ ብሔር ትግሬ
4 ብ/ጄ ጉዕሽ ፅጌ ብሔር ትግሬ
5 ብ/ጄ ገብረኪዳን ገብረማሪያም ብሔር ትግሬ
6 ብ/ጄ ማዕሾ ሃጎስ ብሔር ትግሬ
7 ብ/ጄ ገብሩ ገብረሚካኤል ብሔር ትግሬ
8 ብ/ጄ ማሸሻ ገብረሚካኤል ብሔር ትግሬ
9 ብ/ጄ አብረሃ አረጋይ ብሔር ትግሬ
10 ብ/ጄ ደግፊ ቢዲ ብሔር ትግሬ
11 ብ/ጄ አስካለ ብርሃነ ብሔር ትግሬ
12 ብ/ጄ ሀለፎም እጅጉ ብሔር ትግሬ
13 ብ/ጄ አብርሃ ተስፋዪ ብሔር ትግሬ
14 ብ/ጄ ሙሉ ግርማይ ብሔር ትግሬ
15 ብ/ጄ ወልደ ገብርኤል ባቢ ብሔር ትግሬ
16 ብ/ጄ ፍሰሃ ኪዳነ ማሪያም ብሔር ትግሬ
17 ብ/ጄ አሰፋ ገብሩ ብሔር ትግሬ
18 ብ/ጄ የማነ ሙሉ ብሔር ትግሬ
19 ብ/ጄ ገብረመድህን ፍቃዱ ብሔር ትግሬ
20 ብ/ጄ ታረቀኝ ካሳሁን ብሔር ቅይጥ
21 ብ/ጄ አስራት ዶኖይሮ ብሔር ቅይጥ
22 ብ/ጄ ጥጋቡ ይልማ ብሔር ቅይጥ
23 ብ/ጄ ዘውዱ በላይ ብሔር ቅይጥ
24 ብ/ጄ ኩምሳ ሻንቆ ብሔር ቅይጥ
25 ብ/ጄ አጫሉ ሸለመ ብሔር ቅይጥ
26 ብ/ጄ ሹማ አብደታ ብሔር ቅይጥ
27 ብ/ጄ ድሪባ መኮንን ብሔር ቅይጥ
28 ብ/ጄ ደስታ አብቺ ብሔር ቅይጥ
29 ብ/ጄ አቤል አየለ ብሔር ቅይጥ
30 ብ/ጄ ይመር መኮንን ብሔር ቅይጥ
31 ብ/ጄ ከድር አራርሳ ብሔር ቅይጥ
32 ብ/ጄ ይብራህ ዘሪሁን ብሔር ቅይጥ
33 ብ/ጄ ኩመራ ነጋሪ ብሔር ቅይጥ
34 ብ/ጄ ዱባለ አብዲ ብሔር ቅይጥ
ሜጀር ጄነራል ሆነው የተሾሙት
35 ሜ/ጄ መሐሪ ዘውዴ ብሔር ትግሬ
36 ሜ/ጄ ሐሰን ኢብራሂምና ብሔር ትግሬ
37 ሜ/ጄ መሰለ በለጠ ብሔር ትግሬ

source:www.zehabesha.com

Categories: TPLF woyane